መዝሙር 100 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔርን ለማመስገን የቀረበ ግብዣ

የምስጋና መዝሙር

1. ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤

2. እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤በፍስሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።

3. እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።

4. በምስጋና ወደ ደጆቹ፣በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤

5. እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።