መዝሙር 133 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የወንድማማች ፍቅር

የዳዊት መዝሙረ መዓርግ

1. ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!

2. በራስ ላይ ፈሶ፣እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው።

3. ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአልና።