መዝሙር 93 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእግዚአብሔር ግርማ

1. እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ብርታትንም ታጠቀ፤ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ማንም አይነቀንቃትም።

2. ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ።

4. ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው።

5. ሥርዐትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ቤትህ በቅድስና ይዋባል።