መዝሙር 149 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የድል መዝሙር

1. ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።

2. እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ።

3. ስሙን በሽብሰባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።

4. እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።

5. ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።

6. የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣ባለ ሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤

7. በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤ሰዎችንም ይቀጣሉ፤

8. ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤

9. ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው።ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት።ሃሌ ሉያ።