መዝሙር 117 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የምስጋና ጥሪ

1. አሕዛብ ሁላችሁ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ሕዝቦችም ሁሉ፤ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት፤

2. እርሱ ለእኛ ያሳየው ምሕረት ታላቅ ነውና፤ የእግዚአብሔርም ታማኝነት ጸንቶ ይኖራል።ሃሌ ሉያ።