መዝሙር 131 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በእግዚአብሔር መታመን

የዳዊት መዝሙረ መዓርግ

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።

2. ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኋት፤ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።

3. እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።