መዝሙር 128 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የጻድቃን በረከት

መዝሙረ መዓርግ

1. እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣በመንገዱም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።

2. የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም።

3. ሚስትህ በቤትህ፣እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣እንደ ወይራ ተክል ናቸው።

4. እነሆ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣እንዲህ ይባረካል።

5. እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤

6. የልጅ ልጅ ለማየትም ያብቃህ።በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።