14. እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም።አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ።
15. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብን አበዛህ፤ሕዝብን አበዛህ።ክብሩን ለራስህ አደረግህ፤የምድሪቱንም ወሰን ሁሉ አሰፋህ።
16. እግዚአብሔር ሆይ፤ በተጨነቁ ጊዜ ወደ አንተ መጡ፤በገሠጽሃቸውም ጊዜ፣በለሆሳስ ድምፅ ይጸልያሉ።
17. እግዚአብሔር ሆይ፤ የፀነሰች ሴት ልትወልድ ስትል፣በምጥ እንደምትጨነቅና እንደምትጮኽ፣እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።
18. አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም።
19. ነገር ግን ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤በድናቸውም ይነሣል።እናንት በዐፈር ውስጥ የምትኖሩ፣ተነሡ፤ በደስታም ዘምሩ።ጠልህ እንደ ንጋት ጠል ነው፤ምድር ሙታንን ትወልዳለች።