17. ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤በሩቅ የተዘረጋችውንም ምድር ይመለከታሉ።
18. የቀደመው መከራ ትዝ እያለህ፣“ያ ዋና አለቃ የት አለ?ግብር ተቀባዩስ ወዴት ሄደ?የመጠበቂያ ማማ ኀላፊውስ የት አለ?” ትላለህ።
19. እነዚያ ንግግራቸው የማይገባ፣የሚሉትም የማይታወቅ፣ሊረዱት የማይቻል ቋንቋ የሚናገሩትን ጋጠወጥ ሕዝብ ከእንግዲህ አታያቸውም።
20. በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ካስማዋ የማይነቀል፣ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ።
21. እግዚአብሔር በዚያ ኀይላችን ይሆናል፤ባለ መቅዘፊያ ጀልባዎች እንደማያል ፉባቸው፣ታላላቅ መርከቦችም እንደማይሻገሯቸው፣ሰፋፊ ወንዞችና ጅረቶች ይሆንልናል።
22. እግዚአብሔር ዳኛችን ነው፤ እግዚአብሔር ሕግ ሰጪያችን ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤የሚያድነንም እርሱ ነውና።