ኢሳይያስ 32:14-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤

15. ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስልን፣ምድረ በዳው ለም መሬት፣ለሙ መሬትም ጫካ እስኪመስል ድረስ ነው።

16. በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤

17. የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም መታመን ይሆናል።

18. ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣በሚያስተማምን ቤት፣ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።

19. ደኑ በበረዶ ቢመታ፣ከተማውም ፈጽሞ ቢወድም፣

20. በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣ምንኛ የተባረካችሁ ናችሁ።

ኢሳይያስ 32