5. መጻተኞች የበግ መንጎቻችሁን ያግዳሉ፤ባዕዳን በዕርሻችሁና በወይን ተክል ቦታችሁ ላይ ይሠሩላችኋል።
6. እናንተም የእግዚአብሔር ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤የአምላካችን ባሮች ትባላላችሁ፤የመንግሥታትን ሀብት ትመገባላችሁ፤በብልጽግናቸውም ትኰራላችሁ።
7. ሕዝቤ በኀፍረታቸው ፈንታ፣ዕጥፍ ይቀበላሉ፤በውርደታቸው ፈንታ፣በርስታቸው ደስ ይላቸዋል፤የምድራቸውንም ዕጥፍ ርስት ይወርሳሉ፤ዘላለማዊ ደስታም የእነርሱ ይሆናል።
8. “እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድ፣ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ከእነርሱም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
9. ዘሮቻቸው በመንግሥታት፣ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ፤የሚያዩአቸውም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የባረካቸው ሕዝብ እንደሆኑ ያውቃሉ።