14. እግዚአብሔር፣ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤“የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
15. ሕዝቤን በችግር ስታደቁት፣የድኾችንም ፊት በሐዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?”ይላል ጌታ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
16. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ዐንገታቸውን እያሰገጉ፣በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤እየተቈነኑ በመራመድ፣የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
17. ስለዚህ፣ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይቈረቈር ያመጣል፤ እግዚአብሔርም ራሳቸውን ቡሀ ያደርጋል።
18. በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፣ የጠጒር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፣
19. የጆሮ ጒትቻውን፣ የእጅ አንባሩን፣ የፊት መሸፈኛውን፣
20. የራስ መሸፈኛውን፣ ዐልቦውን፣ ሻሹን፣ የሽቶ ብልቃጡን፣ አሸንክታቡን፣
21. የጣት ቀለበቶችንና የአፍንጫ ቀለበቶችን፣
22. ያማረውን ቀሚስ፣ የውስጥ ልብሱን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣
23. መስታወቱን፣ ከጥሩ በፍታ የተሠራውን ልብስ፣ የራስ ጌጡን፣ ዐይነ ርግቡን ሁሉ ይነጥቃቸዋል።
24. በሽቶ ፈንታ ግማት፣በሻሽ ፈንታ ገመድ፣አምሮ በተሠራ ጠጒር ፈንታ ቡሀነት፣ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል።
25. ወንዶቻችሁ በሰይፍ ስለት፣ተዋጊዎቻችሁ በጦርነት ይወድቃሉ።
26. የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።