15. ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ለሚወርዱሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣“ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው!
16. እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ፤ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣“እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን?ሸክላ የሠራውን፣“እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን?
17. ሊባኖስ ወደ ለም ዕርሻነት ለመለወጥ፣ለም የሆነውም መሬት ወደ ዱርነት ለመለወጥ ጥቂት ጊዜ አልቀረውምን?
18. በዚያን ጊዜ ደንቈሮ የጥቅልሉን መጽሐፍ ቃል ይሰማል፤የዐይነ ስውሩም ዐይኖችከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።
19. ትሑታን በእግዚአብሔር፣ምስኪኖችም በእስራኤል ቅዱስ እንደ ገና ሐሤት ያደርጋሉ።
20. ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ፌዘኞችም በነው ይጠፋሉ፤ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ።
21. ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፣በተከሳሽ ላይ ወጥመድ የሚዘረጉ፣በሐሰት ምስክር ፍትሕን ከንጹሓን የሚቀሙ ይቈረጣሉ።
22. ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔርለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤“ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።
23. በመካከላቸው የእጄ ሥራ የሆኑ፣ልጆቻቸውን ሲያዩ፣ስሜን ይቀድሳሉ፤የያዕቆብን ቅዱስ ቅድስና ያውቃሉ፤በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሀት ይቆማሉ።
24. በመንፈስ የሳቱ ያስተውላሉ፤የሚያጒረመርሙም ምክር ይቀበላሉ።”