18. አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም።
19. ነገር ግን ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤በድናቸውም ይነሣል።እናንት በዐፈር ውስጥ የምትኖሩ፣ተነሡ፤ በደስታም ዘምሩ።ጠልህ እንደ ንጋት ጠል ነው፤ምድር ሙታንን ትወልዳለች።
20. ሕዝቤ ሆይ፤ ሂድ ወደ ቤትህ ግባ፤በርህን ከኋላህ ዝጋ፤ቍጣው እስኪያልፍ ድረስ፣ለጥቂት ቀን ተሸሸግ።
21. በምድር ላይ የሚኖረውን ሕዝብ ስለ ኀጢአቱ ለመቅጣት፣እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያው ወጥቶ ይመጣል፤ምድር በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤የተገደሉትንም ከእንግዲህ አትሸሽግም።