መዝሙር 133:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!

2. በራስ ላይ ፈሶ፣እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው።

3. ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአልና።

መዝሙር 133