ኢሳይያስ 24:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ምድር ተከፈለች፤ምድር ተሰነጠቀች፤ምድር ፈጽማ ተናወጠች።

20. ምድር እንደ ሰካራም ዞረባት፤ነፋስ እንደሚወዘውዘውም ጐጆ ሆነች፣የዐመጿ ሸክም ከባድ ስለ ሆነ ትወድቃለች፤እንደ ገናም አትነሣም።

21. በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣በላይ በሰማያት ያሉትን ኀይሎች፣በታችም በምድር ያሉትን ነገሥታት ይቀጣቸዋል።

22. በጒድጓድ ውስጥ እንዳሉ እስረኞች፣በአንድ ላይ ይታጐራሉ፤በእስር ቤት ይዘጋባቸዋል፣ከብዙ ቀንም በኋላ ለፍርድ ይቀርባሉ።

23. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣በሽማግሌዎቹም ፊት በክብሩ ይነግሣል፤ጨረቃ ትሸማቀቃለች፤ ፀሓይም ታፍራለች።

ኢሳይያስ 24