ኢሳይያስ 18:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በኢትዮጵያ ወንዞች ዳር ለምትገኝ፣ፉር ፉር የሚሉ ክንፎች ላሉባት ምድር ወዮላት!

2. ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት።እናንት ፈጣን መልእክተኞች፤ረጃጅምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!

3. እናንት የዓለም ሕዝቦች፣በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።

4. እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“ጸጥ ብዬ እቀመጣለሁ፤ከማደሪያዬም በፀሓይ ሐሩር እንደሚያ ብረቀርቅ ትኵሳት፣በመከርም ሙቀት እንደ ደመና ጠል ሆኜ እመለከታለሁ።”

ኢሳይያስ 18