10. የሰማይ ከዋክብትና ሰራዊታቸው፣ብርሃን አይሰጡም፤ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።
11. ዓለምን ስለ ክፋቷ፣ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤የጨካኞችንም ጒራ አዋርዳለሁ።
12. ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፣ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።
13. ስለዚህ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ቍጣው በሚነድበት ቀን፣ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ።
14. እንደሚታደን ሚዳቋ፣እረኛም እንደሌለው የበግ መንጋ፣እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።
15. የተማረከ ሁሉ ይወጋል፤የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።
16. ዐይናቸው እያየ ሕፃናታቸው ይጨፈጨፋሉ፤ቤታቸው ይዘረፋል፤ ሚስቶቻቸው ይደፈራሉ።
17. እነሆ፤ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣በወርቅም ደስ የማይሰኙትን፣ሜዶናውያንን አስነሣባቸዋለሁ።
18. ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ሕፃናትን አይምሩም፤ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።
19. የመንግሥታት ዕንቍ፣የከለዳውያን ትምክሕት፣የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል።
20. በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤የሚቀመጥባትም የለምዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም።
21. ነገር ግን የምድረ በዳ አራዊት በዚያ ይተኛሉ፤ቀበሮዎች ቤቶቿን ይሞላሉ፤ጒጒቶች በዚያ ይኖራሉ፤በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም ይዛለሉበታል።