አሞጽ 5:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤

2. “ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ከእንግዲህም አትነሣም፤በገዛ ምድሯ ተጣለች፤የሚያነሣትም የለም።”

3. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“አንድ ሺህ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።”

4. እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”

5. ቤቴልን አትፈልጉ፤ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤ጌልገላ በእርግጥ ትማረካለች፤ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና።

6. እግዚአብሔርን ፈልጉ፤በሕይወትም ትኖራላችሁ፤አለበለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።

አሞጽ 5