ማሕልየ መሓልይ 6:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

8. ሥልሳ ንግሥቶች፣ሰማንያ ቁባቶች፣ቊጥራቸውም የበዛ ደናግል ሊኖሩ ይችላሉ፤

9. እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፤ለእናቷም አንዲት ናት፤ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ”አሏት፤ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት።

10. እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?

11. በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀሉትን አትክልቶች ለማየት፣ወይኑ ማቈጥቈጡን፣ሮማኑ ማበቡን ለመመልከት፣ወደ ለውዙ ተክል ቦታ ወረድሁ።

12. ይህን ከማወቄ በፊት፣ምኞቴ በሕዝቤ ንጉሣዊ ሠረገሎች መካከል አስቀመጠኝ።

ማሕልየ መሓልይ 6