1. ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ?አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?
2. አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣ጥፋትን ያውጠነጥናል።
3. ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ። ሴላ
4. አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!
5. እግዚአብሔር ግን ለዘላለምያንኰታኵትሃል፤ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ
6. ጻድቃን ይህን ዐይተው ይፈራሉ፤እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
7. “እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣በክፋቱም የበረታ፣ያ ሰው እነሆ!”