መዝሙር 51:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።

15. ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት፤አፌም ምስጋናህን ያውጃል።

16. መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ ባቀረብሁልህ ነበር፤የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም።

17. እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤እግዚአብሔር ሆይ፤አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።

18. በበጎ ፈቃድህ ጽዮንን አበልጽጋት፤የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ።

መዝሙር 51