14. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እንድትድኚ ከልብሽ ክፋት ታጠቢ፤እስከ መቼ ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ ይኖራል?
15. ድምፅ ከዳን ይሰማልና፤ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል።
16. “ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤‘ከበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤
17. ሰብል እንደሚጠብቁ ሰዎች ይከቧታል፤በእኔ ላይ ዐምፃለችና፤’ ”ይላል እግዚአብሔር።
18. “የገዛ መንገድሽና ተግባርሽ፣ይህን አምጥቶብሻል፤ይህም ቅጣትሽ ነው፤ምንኛ ይመራል!እንዴትስ ልብ ይሰብራል!”
19. ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ!ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤አወይ፣ የልቤ ጭንቀት!ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ዝም ማለት አልችልም፤የመለከትን ድምፅ፣የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና።
20. ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል፤ምድሪቱም በሞላ ባድማ ትሆናለች፤ድንኳኔ በድንገት፣መጠለያዬም በቅጽበት ጠፋ።
21. እስከ መቼ የጦርነት ዐርማ እመለከታለሁ?እስከ መቼስ የመለከት ድምፅ እሰማለሁ?
22. “ሕዝቤ ተላሎች ናቸው፤እኔን አያውቁኝም።ማስተዋል የጐደላቸው፣መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው።ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፤መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”