12. የሟቾች ጣር ጩኸት ከከተማዋ ይሰማል፤የቈሰሉት ሰዎች ነፍስ ለርዳታ ይጮኻል፤እግዚአብሔር ግን ተጠያቂዎቹን ዝም ብሎአል።
13. “በብርሃን ላይ የሚያምፁ፣ጐዳናውን የማያውቁ፣በመንገዱም የማይጸኑ አሉ።
14. ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ድኾችንና ችግረኞችን ይገድላል፤በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤
15. አመንዝራ በዐይኑ ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤‘ማንም አያየኝም’ ብሎ ያስባል፤ፊቱንም ይሸፍናል።
16. በጨለማ፣ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ብርሃንንም አይፈልጉም።
17. ድቅድቅ ጨለማ ለሁላቸው እንደ ንጋት ነው፤አሸባሪውን ጨለማ ይወዳጃሉ።
18. “ይሁን እንጂ፣ በውሃ ላይ የሚኵረፈረፍ ዐረፋ ናቸው፤የወይን ቦታው ሰው የማይደርስበት፣ርስታቸው ርጉም ነው።
19. ድርቅና ሙቀት የቀለጠውን በረዶ ከቦታው እንደሚያስወግድ፣ሲኦልም ኀጢአተኞችን ትነጥቃለች።
20. የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤የሚያስታውሳቸውም የለም።
21. የማትወልደውን መካኒቱን ይቦጠቡጣሉ፤ለመበለቲቱም አይራሩም።
22. ነገር ግን እግዚአብሔር ብርቱዎችን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም።
23. ያለ ሥጋት እንዲኖሩ ትቶአቸው ይሆናል፤ዐይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው።
24. ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሆኖም ይጠፋሉ፤ዝቅ ዝቅ ብለው፤ እንደ ሌሎቹ ይከማቻሉ።እንደ እህል ራስም ይታጨዳሉ።
25. “ይህ እንዲህ ካልሆነማ፣ የሚያስተባብለኝ ማን ነው?ቃሌን ከንቱ የሚያደርገውስ ማን ነው?”