13. ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤እናንት በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤የእህል ቊርባኑና የመጠጥ ቊርባኑ፣ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጦአልና።
14. ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤የተቀደሰንም ጉባኤ ጥሩ፤ሽማግሌዎችን ሰብስቡ፤በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ፣ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ጥሩ፤ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።
15. ወዮ ለዚያ ቀን፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፤ሁሉን ከሚችል አምላክ እንደ ጥፋት ይመጣል።
16. የሚበላ ምግብ፣ከዐይናችን ፊት፣ደስታና ተድላ፣ከአምላካችን ቤት አልተቋረጠብንምን?
17. ዘሩ በዐፈር ውስጥ፣በስብሶ ቀርቶአል፤ግምጃ ቤቶቹ ፈራርሰዋል፤ጐተራዎቹም ተሰባብረዋል፤እህሉ ደርቆአልና።
18. መንጎች እንደ ምን ጮኹ፣ከብቶቹ ተደናግጠዋል፤መሰማሪያ የላቸውምና፤የበግ መንጎች እንኳ ተቸግረዋል።
19. አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ያልተነካውን መሰማሪያ እሳት በልቶታልና፤የዱሩን ዛፍ ሁሉ፣ ነበልባል አቃጥሎታል።
20. የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ አለኸለኹ፤ወራጁ ውሃ ደርቆአል፤ያልተነካውንም መሰማሪያ፣ እሳት በልቶታል።