ኢሳይያስ 60:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና።

20. ፀሓይሽ ከእንግዲህ አትጠልቅም፤ጨረቃሽም ብርሃን መስጠቷን አታቋርጥም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል፤የሐዘንሽም ቀን ያከትማል።

21. ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ፤ለክብሬ መግለጫ ይሆኑ ዘንድ፣የእጆቼ ሥራ፣እኔ የተከልኋቸው ቊጥቋጦች ናቸው።

22. ከአንቺ ታናሽ የሆነው ሺህ፣ከሁሉም የመጨረሻው ታናሽ ኀያል መንግሥት ይሆናል፤እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ጊዜውም ሲደርስ ይህን በፍጥነት አደርጋለሁ።”

ኢሳይያስ 60