1. ጻድቅ ይሞታል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣መወሰዳቸውን፣ማንም አያስተውልም።
2. በቅንነት የሚሄዱ፣ሰላም ይሆንላቸዋል፤መኝታቸው ላይ ያርፋሉ።
3. “እናንት የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣እናንት የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤ እናንት፣ ወዲህ ኑ፤
4. የምትሣለቁት በማን ላይ ነው?የምታሽሟጥጡት ማንን ነው?ምላሳችሁንስ አውጥታችሁ የምታሾፉት በማን ላይ ነው?እናንት የዐመፀኞች ልጆች፣የሐሰተኞች ዘር አይደላችሁምን?