1. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እናታችሁን የፈታሁበትየፍቺ ወረቀት የት አለ?ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁለየትኛው አበዳሪዬ ነው?እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈታለች።
2. በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም?በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ?ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ አጥራ ነበርን?እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን?እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤በጥማትም ይሞታሉ።
3. ሰማይን ጨለማ አለብሰዋለሁ፤ማቅን መሸፈኛው አደርጋለሁ።