ኢሳይያስ 32:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ።

2. እያንዳንዱ ሰው ከነፋስ መከለያ፣ከወጀብም መጠጊያ ይሆናል።በበረሓም እንደ ውሃ ምንጭ፣በተጠማም ምድር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።

3. የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያዳምጣሉ።

4. የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤አጥርቶም ይናገራል።

ኢሳይያስ 32