2. ጀግናውንና ተዋጊውን፣ፈራጁንና ነቢዩን፣አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣
3. የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፣አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለ ሙያ፣ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።
4. ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።
5. ሕዝብ እርስ በርሱ ይጨቋቈናል፤ሰው በሰው ላይ፤ ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ፣ወጣቱ በሽማግሌው ላይ፣ተራው ሰው በተከበረው ላይ ይነሣል።
6. ሰውም በአባቱ ቤትከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፣“አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ይህንንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል።
7. እርሱ ግን በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣“እኔ መፍትሔ አልሆንም፤በቤቴም ልብስና ምግብ የለኝም፤የሕዝብ መሪ አታድርጉኝ” ይላል።
8. ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።
9. የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤አይደብቁትምም፤ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ።ወዮላቸው!
10. ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና።
11. በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋትይመጣባቸዋል፤የእጃቸውን ያገኛሉና።