1. እነሆ፤ ጌታ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርከኢየሩሳሌምና ከይሁዳድጋፉንና ርዳታውን፣የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤
2. ጀግናውንና ተዋጊውን፣ፈራጁንና ነቢዩን፣አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣
3. የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፣አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለ ሙያ፣ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።
4. ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።
5. ሕዝብ እርስ በርሱ ይጨቋቈናል፤ሰው በሰው ላይ፤ ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ፣ወጣቱ በሽማግሌው ላይ፣ተራው ሰው በተከበረው ላይ ይነሣል።