ኢሳይያስ 29:17-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ሊባኖስ ወደ ለም ዕርሻነት ለመለወጥ፣ለም የሆነውም መሬት ወደ ዱርነት ለመለወጥ ጥቂት ጊዜ አልቀረውምን?

18. በዚያን ጊዜ ደንቈሮ የጥቅልሉን መጽሐፍ ቃል ይሰማል፤የዐይነ ስውሩም ዐይኖችከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።

19. ትሑታን በእግዚአብሔር፣ምስኪኖችም በእስራኤል ቅዱስ እንደ ገና ሐሤት ያደርጋሉ።

20. ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ፌዘኞችም በነው ይጠፋሉ፤ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ።

21. ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፣በተከሳሽ ላይ ወጥመድ የሚዘረጉ፣በሐሰት ምስክር ፍትሕን ከንጹሓን የሚቀሙ ይቈረጣሉ።

22. ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔርለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤“ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።

23. በመካከላቸው የእጄ ሥራ የሆኑ፣ልጆቻቸውን ሲያዩ፣ስሜን ይቀድሳሉ፤የያዕቆብን ቅዱስ ቅድስና ያውቃሉ፤በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሀት ይቆማሉ።

24. በመንፈስ የሳቱ ያስተውላሉ፤የሚያጒረመርሙም ምክር ይቀበላሉ።”

ኢሳይያስ 29