ኢሳይያስ 10:23-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል።

24. ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤“በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤ግብፅ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፣በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው።

25. በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤በእነርሱም ላይ መቅሠፍቴን አመጣለሁ።”

26. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደመታ፣በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤በግብፅ እንዳደረገውም ሁሉ፣በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።

27. በዚያን ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ከውፍረትህም የተነሣቀንበሩ ይሰበራል።

28. ወደ ዐያት ይገባሉ፣በሚግሮን ያልፋሉ፤ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ።

29. መተላለፊያውን ዐልፈው እንዲህ ይላሉ፤“በጌባዕ ሰፍረን እናድራለን።”ራማ ደነገጠች፤የሳኦል ከተማ ጊብዓ ሸሸች።

30. የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺላይሻ ሆይ፤ አድምምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ መልሺላ

31. ማድሜናህ በሽሽት ላይ ነች፤የጌቢም ሕዝብ ሊደበቅ ይሮጣል።

32. በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻነቀነቁ።

33. እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በታላቅ ኀይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤ረጃጅም ዛፎች ይገነደሳሉ፤ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።

ኢሳይያስ 10