ሚክያስ 4:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. አሁን ግን ብዙ አሕዛብ፣በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል፤እነርሱም፣ “የረከሰች ትሁን፤ዐይናችንም ጽዮንን መዘባበቻ አድርጎ ይያት” ይላሉ።

12. ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሐሳብ አያውቁም፤በአውድማ ላይ እንደ ነዶየሚሰበስባቸውን፣የእርሱን ዕቅድ አያስተውሉም።

13. የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ተነሥተሽ አበራዪ፤የብረት ቀንድ እሰጥሻለሁና፤የናስ ሰኰና እሰጥሻለሁ፤አሕዛብንም ታደቂያቸዋለሽ።”በግፍ ያግበሰበሱትን ትርፍ ለእግዚአብሔር፣ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ታቀርቢያለሽ።

ሚክያስ 4