መዝሙር 99:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤በእግሩ መርገጫ ስገዱ፤እርሱ ቅዱስ ነውና።

6. ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤እርሱም መለሰላቸው።

7. ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።

8. እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤አንተ መለስህላቸው፤ጥፋታቸውን ብትበቀልም እንኳ፣አንተ ይቅር የምትላቸው አምላክ ነህ።

9. አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤በቅዱስ ተራራውም ላይ ስገዱ፤አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

መዝሙር 99