መዝሙር 59:15-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ።ካልጠገቡም ያላዝናሉ።

16. እኔ ግን ስለ ኀይልህ እዘምራለሁ፤በማለዳም ስለ ምሕረትህ እዘምራለሁ፤አንተ መጠጊያዬ፣በመከራም ቀን ዐምባዬ ነህና።

17. ብርታቴ ሆይ፤ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ፤እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ፣የምትወደኝም አምላኬ ነህና።

መዝሙር 59