6. ጻድቃን ይህን ዐይተው ይፈራሉ፤እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
7. “እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣በክፋቱም የበረታ፣ያ ሰው እነሆ!”
8. እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት፣እንደለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤ከዘላለም እስከ ዘላለም፣በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።
9. ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ስምህ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።