መዝሙር 42:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤አዳኜና

6. አምላኬን፣ ገና አመሰግነዋለሁና።ነፍሴ በውስጤ ተክዛለች፤ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር፣በአርሞንኤም ከፍታ፣ በሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።

7. በፏፏቴህ ማስገምገም፣አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል፤ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቀኝ።

8. እግዚአብሔር ምሕረቱን በቀን ያዝዛል፤ዝማሬውም በሌሊት በእኔ ዘንድ አለ፤ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው።

መዝሙር 42