8. ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ።
9. ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።
10. ክንድህን አንሣልኝ፤ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁና።
11. ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ
12. “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ጩኸቴን አድምጥ፤ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ።