መዝሙር 19:8-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ዐይንን ያበራል።

9. እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ሁለንተናውም ጻድቅ ነው፤

10. ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።

11. ደግሞም አገልጋይህ በእርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው።

12. ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል?ከተሰወረ በደል አንጻኝ።

13. ባሪያህን ከድፍረት ኀጢአት ጠብቅ፤እንዳይሠለጥንብኝም ርዳኝ፤ያን ጊዜ ያለ እንከን እሆናለሁ፤ከታላቅ በደልም እነጻለሁ።

14. መጠጊያዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣በፊትህ ያማረ ይሁን።

መዝሙር 19