መዝሙር 125:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት፣ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።

3. ጻድቃን እጃቸውን፣ ለክፋት እንዳያነሡ፣የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ለሆኑ፣ልባቸውም ለቀና መልካም አድርግ።

5. ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል።በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።

መዝሙር 125