መዝሙር 110:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ጌታዬን፣“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ፣እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” አለው።

2. እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል፤አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።

3. ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ከንጋት ማሕፀን፣በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣የጐልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።

4. “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሎአል፤እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።

5. ጌታ በቀኝህ ነው፤በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቃቸዋል።

መዝሙር 110