መክብብ 11:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።

2. ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።

3. ደመናት ውሃ ካዘሉ፣በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።

መክብብ 11