ሕዝቅኤል 19:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ስለ እስራኤል መሳፍንት ሙሾ አውጣ፤

2. እንዲህም በል፤“ ‘እናትህ በአንበሶች መካከል እንዴትያለች አንበሳ ነበረች!በደቦል አንበሶች መካከል ተጋደመች፤ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች።

3. ከግልገሎቿ መካከል አንዱን አሳደገችው፤እርሱም ብርቱ አንበሳ ሆነ።ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ሰዎችንም በላ።

4. አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤በጒድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ፤እነርሱም በስናግ ጐትተው፣ወደ ግብፅ ምድር ወሰዱት።

5. “ ‘ተስፋዋ መጨናገፉን፣የጠበቀችውም አለመሳካቱን ባየች ጊዜ፣ከግልገሎቿ ሌላውን ወስዳ፣ብርቱ አንበሳ አድርጋ አሳደገችው።

6. እርሱም በአንበሶች መካከል ተጐማለለ፤እየበረታም ሄደ፤ግዳይ መንጠቅን ተማረሰዎችንም በላ።

7. ምሽጎቻቸውን አወደመ፤ከተሞቻቸውንም ባድማ አደረገ፤ምድሪቷና በውስጧ ያሉት ሁሉ፣ከግሣቱ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።

8. በዙሪያው ያሉ አሕዛብ ተነሡበት፤ከየአገሩም ሁሉ ተሰበሰቡበት፤መረባቸውን ዘረጉበት፤በጒድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ።

ሕዝቅኤል 19