ዘካርያስ 9:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፎአልና።

2. ደግሞም በአዋሳኟ በሐማት፣ጥበበኞች ቢሆኑም እንኳ በጢሮስና በሲዶና ላይ ያርፍባቸዋል።

3. ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ብሩን እንደ ዐፈርወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።

ዘካርያስ 9