41. ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ትእዛዝ ለምን ትጥሳላችሁ? ይህም አይሳካላችሁም!
42. እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእናንተ ጋር ስላይደለ አትውጡ፤ በጠላቶቻችሁ ድል ትመታላችሁ፤
43. አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በዚያ ያጋጥሟችኋልና። እግዚአብሔርን (ያህዌ) ስለተዋችሁትና እርሱም ከእናንተ ጋር ስለማይሆን በሰይፍ ትወድቃላችሁ።”
44. ሙሴም ሆነ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ታቦት ከሰፈር ሳይነሡ በስሜት ተገፋፍተው ብቻ ወደ ተራራማው አገር ወጡ።
45. በዚህ ጊዜ በተራራማው አገር የሚኖሩት አማሌቃውያንና ከነዓናውያን ወርደው ወጉአቸው፤ እስከ ሔርማ ድረስም አሳደዱአቸው።