25. ጠላት ሰይፍ ታጥቆአል፤በየቦታውም ሽብር ሞልቶአል፤ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤በየመንገዱ አትዘዋወሩ።
26. የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ምርር ብለሽ አልቅሺ፤አጥፊው በድንገት፣በላያችን ይመጣልና።
27. “ብረት እንደሚፈተን፣የሕዝቤን መንገድ፣አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።
28. ሁሉም ለማማት የሚዞሩ፣ድድር ዐመፀኞች፣ናስና ብረት የሆኑ፣ምግባረ ብልሹዎች ናቸው።
29. ርሳሱን ለማቅለጥ፣ወናፉ በብርቱ አናፋ፤ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና።
30. እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና፣የተናቀ ብር ተብለው ይጠራሉ።