22. ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤“በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን?ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።
23. ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልከኛ ልብ አለው፤መንገድ ለቆ ሄዶአል፤
24. በልባቸውም፣‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።
25. በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል።ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሎአችኋል።
26. “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።
27. ወፎች እንደሞሉት ጐጆ፣ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤