ኤርምያስ 23:22-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ምክሬ ባለበት ቢቆሙ ኖሮ፣ቃሌን ለሕዝቤ ባሰሙ ነበር፤ከክፉ መንገዳቸው፣ከክፉ ሥራቸውም በመለሷቸው ነበር።

23. “እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝን?ይላል እግዚአብሔር፤“የሩቅስ አምላክ አይደለሁምን?

24. እኔ እንዳላየው፣በስውር ቦታ ሊሸሸግ የሚችል አለን?”ይላል እግዚአብሔር።“ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን”ይላል እግዚአብሔር።

25. “ ‘ሕልም አለምሁ ሕልም አለምሁ’ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩትን የነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ፤

ኤርምያስ 23