እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”